ፕሬዚዳንት ባይደን የሩሲያውን ቭላዲሚር ፑቲንን አውግዘዋል

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባይደን “ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን” በተሰኘው የትናንት ምሽቱ የመጀመሪያ የሃገራቸው ሁኔታ ንግግር ዩክሬንን የወረሩትን የሩሲያውያን ፕሬዚዳንት ቫላድሚር ፑቲንን አውግዘው የሁሉንም ወገኖች የተባበረ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

ከወረርሽኙ እያገገመ ያለውን ምጣኔ ሐብት በመጉዳት እየጨመረ ስለመጣው የዋጋ ግሽበትም ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም የምክር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ድጋፍ ያስገኛል ያሉትን “የጋራ” አጀንዳዎቻቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡