በደቡብ ክልል በህገ ወጥ ግንባታና በመሬት ወረራ ተሳትፈዋል የተባሉ ኃላፊዎች ዕርምጃ ተወሰደ

Your browser doesn’t support HTML5

በህገ ወጥ ግንባታና በመሬት ወረራ ተሳትፈዋል ባላቸው ከ40 በላይ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የደቡብ ክልል የቤቶችና ከተማ ልማት ቢሮ አስታውቋል። መንግሥት ያወጣውን የመሬት አጠቃቀም ፖሊስና ስልት ባለመከተሉ በአብዛኞቹ የክልሉ ከተሞች የመሬት አቅርቦትና አስተዳደር ሥርዓት በብልሹ አሰራርና በሌብነት የተተበተቡ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናግረዋል። ቢሮ ይህንን ያስታወቀው በሃዋሳ ከተማ ባካሄደው የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።