ደቡብ ሱዳናዊያን አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠዋል

Germaniya

የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ዛሬ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ገብተዋል፡፡



አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ


Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ ሱዳናዊያን አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠዋል፤ በሽር ጁባ ናቸው


የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ዛሬ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ገብተዋል፡፡

የአል-በሽር ጉዞ ዓላማ በድርድሩ ላይ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ለመነጋገር መሆኑም ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ያለው ድርድር የሚካሄደው በምሥጢር መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ወገኖቹ ወደዋናው ድርድራቸው ከመግባታቸው በፊት የጋራ በሚባሉ ግጭቶችን በማቆም እና የእሥረኞችን መፈታት በሚመለከቱ አቋሞች ላይ ለመነጋገር መቀመጣቸውንና ውጤቱ ማምሻውን እየተጠበቀ መሆኑን አምባሣደር ዲና ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር ዘገባውንና ከአምባሣደር ዲና ሙፍቲ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ የያዘውን ፋይል ያዳምጡ፡፡