ደቡብ ሱዳን - እንደገና ጦርነት፤ እንደገና ስደት …

ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ

በደቡብ ሱዳን ሁለት ስቴቶች ወይም ክልሎች ውስጥ በተቀሰቀሰ ከባድ ውጊያና በረሃብ ምክንያት ከመቶ ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናዊያን ባለፉ ሁለት ወራት ውስጥ መፈናቀላቸውንና መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታውቋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች /ፎቶ ፋይል/

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ ሱዳን - እንደገና ጦርነት፤ እንደገና ስደት …

በደቡብ ሱዳን ሁለት ስቴቶች ወይም ክልሎች ውስጥ በተቀሰቀሰ ከባድ ውጊያና በረሃብ ምክንያት ከመቶ ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናዊያን ባለፉ ሁለት ወራት ውስጥ መፈናቀላቸውንና መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታውቋል፡፡

ከደቡብ ሱዳን ከሚሰደዱት ከዘጠና ዘጠኝ ከመቶው በላይ የሚገቡት ወደ ኢትዮጵያ መሆኑንና የደቡብ ሱዳን ግጭት ከተጫረ ከታኅሣስ 2006 ዓ.ም ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ 208 ሺህ 700 የሚሆኑ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን በኢትዮጵያ የዩኤንኤችሲአር ቃልአቀባይ አቶ ክሡት ገብረእግዚአብሄር ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ - ኩሌ መጠለያ /ፎቶ ፋይል/

በሌላ በኩል ደግሞ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለሚገኙት ሽምቅ ተዋጊዎች፣ ከአየር ጦር መሣሪያ እያቀበለች ናት ሲል አንድ ሰሞኑን የወጣ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ኻርቱም ግን «በዚህ ውዝግብ እጄ የለበትም» ስትል አስተባብላለች።

የተባለው ጦር መሣሪያ የማቀበሉ ሂደት፣ በመንግሥቱና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል እአአ በ2013 የተቀሰቀሰው ውጊያ እንዲቀጥል አድርጎታል ሱሉ ተንታኞች ይናገራሉ።

የደቡብ ሱዳን ተዋጊዎች /ፎቶ ፋይል/

ለዝርዝሩ ዘገባዎቹን የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡