በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የሰሩበትን ደመወዝ የተከለከሉ የመንግሥት ሠራተኞች ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ መጋለጣቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ስለማይከፈላቸው አንዳንድ መምህራን የተማሩባቸውና ሲያገለግሉበት የነበረውን ሞያ ትተው በግብርና ሥራ መሰማራታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ::

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ውስጥ በሚገኙ 21 ወረዳዎች ተቀጥረው በማገልገል ላይ የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸው ለረዥም ጊዜ በመቁረጡ ለኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች ተጋለጣቸውን አስረድተዋል::

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ብቻ ከ3ሺህ በላይ ሠራተኞች ለወራት ደመወዛቸው ባለመከፈሉ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንደተሳናቸውና ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ዘርዝረዋል::

ከደሞዝ አለመከፈል ጋር በተያያዘ በዳሞት ወይዴ ወረዳ ያሉ አራት ጤና ጣቢያዎች እና አንድ ሆስፒታል በመሉ አቅሙ አገልግሎቶችን እየሰጡ አለመኾናቸው እና በዚህም የተነሳ የአከባቢው ማህበረሰብ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን የማግኘት መብት መጣሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትላትናው ዕለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል::