ጆሃንስበርግ ላይ ሠልፍ ተደረገ

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
    ቪኦኤ ዜና

ጃከብ ዙማ - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት /ፎቶ - ፋይል/

ፕሬዚዳንት ዙማ መጤ-ጠል ጥቃቱን አወገዙ፡፡

/ፎቶ - ፋይል/

Your browser doesn’t support HTML5

ጆሃንስበርግ ላይ ሠልፍ ተደረገ

በደቡብ አፍሪካይቱ ደርባን ከተማ ካለፈው ሣምንት ዓርብ ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን በመቃወም በበርካታ ሺሆች የተቆጠሩ ደቡብ አፍሪካዊያንና ሌሎች ፍልሰተኞች ዛሬ፤ ሐሙስ - ሚያዝያ 8/2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ አካሂደዋል።

“አፍሪካ አንድ ናት፤ የጥላቻ ጥቃት ይቁም” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው እያሰሙም ነበር ሠልፈኞቹ፡፡

አንድ ኢትዮጵያዊን ጨምሮ በትንሹ ለአምስት ሰዎች ህይወት መጥፋት እንዲሁም ለበርካቶች መቁሰልና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ሁከት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ ዛሬ አውግዘዋል።

ግጭቱን በመሥጋት በጆሃንስበርግ ከተማ አንዳንድ ሠፈሮች እንዲሁም ደርባን ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያዊያንና የሌሎችም ሀገሮች ዜጎች የንግድ ተቋማት ዛሬ ተዘግተው ውለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡