ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ኮሌራ ብዙ ሰው ገደለ

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ አቅራቢያ የኮሌራ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከሃያ የሚበልጡ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የተቆጠሩ ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጠ፡፡ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ወረርሽኙ እንዴት እንደተቀሰቀሰ በመከታተል ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የሃማንስክራል ከተማ ነዋሪዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት በበኩላቸው መንግሥቱን ተጠያቂ አድርገዋል።