የሰልፉ ዓላማ በግድያው ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና ስለድንገቱ የኢትጵያ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ ለመጠየቅ መሆኑን ከሰልፉ ተካፋዮች አንዱ አሊ ሳአድ ዓብደልቃዲ ሲያስረዱ እ.አ.አ. ሰኔ 5 ቀን ጂማዎ ዱብቲ ውስጥ ስለተፈጸመው ፍጅት ተቃውሟችንን ለመግለጽ ነው። ያለነው ነጻ ሃገር ነው ስለዚህ የሚሰማንን እየተናገርን ነው ብለዋል።
ሳሃል ዩሱፍ የተባሉ ሌላ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ስለግድያው ማብራሪያ እንዲሰጥ በመጠየቅ የእቤቱታ ደብዳቤ ፈርመናል ደብዳቤውን ወደሄጉ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) እናቀርባለን ማለታቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ፋራህ ኣሊ የተባሉና በሰልፉ ለመካፈል ከበርሚንግሃም ወደለንደን መጓዛቸውን የገለጹ ተሳታፊ በበኩላቸው ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የትውልድ ከተማቸው መሆኑን ገልጸው ከተገደሉት መካከል ልጆች አረጋውያንና ነፍሰ ጡር ሴቶች አሉባቸው ብለዋል። በሮማዳን የመጀመሪያ ቀን የተፈጸውምን ጥቃት ያደረሱት የኢትዮጳያ ክልል አምስት ፖሊሶችና ልዩ ፖሊስ ሃይሎች ናቸው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
Your browser doesn’t support HTML5
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ምላሽ ለማግኘት የሶማሊኛ ክፍል ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጿል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5