የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እና አንድምታው

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያ ፓርላማ በትላንትናው እለት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድን አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። የ67 አመቱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ለዚያች አገር ፖለቲካ አዲስ አይደሉም።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከመስከረም 2012 አንስቶ እስከ የካቲት 2017 ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ተሸንፈው እስከወጡበት ጊዜ ድረስ ሶማሊያን በፕሬዚዳንትነት መርተዋል።

የምርጫው ውጤት በሃገሪቱም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ላይ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ ተንታኝ አነጋግረናል።