ሞቅዲሾ የደረሰው ፍንዳታ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ቅዳሜ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የደረሰው ፍንዳታ፣ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ። ነዋሪዎች በጥቃቱ የተሰማቸውን ቁጣ ለመግለፅ፣ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውም ታውቋል፣ ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን ማውገዛ ታውቋል። በቅዳሜው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 276 መድረሱን፣ የቆሰሉት ደግሞ 429 እንደሆኑ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አብድራህማን ኦስማን ገልፀዋል፡፡