የሶማሌ ክልል በግለሰቦች እጅ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን መሰብሰብ ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎችና የሚመለከታቸው አካላት በስተቀር በሌሎች የክልሉ ነዋሪዎች እጅ የሚገኙ የጦር መሳሪያዎችን መሰብሰብ ጀምሬያለሁ ብሏል። አሁን በተመረጠ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ይህ የጦር መሳሪያ ስብሰባ ወደፊት በሁሉም የክልሉ ዞኖች ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል። የውሳኔው መነሻ በጎሳ ግጭት የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑ ነው ተብሏል።