ህብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ
Your browser doesn’t support HTML5
ህብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ የምርጫ ቦርድ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የምርጫ ካርታ ተቃወመ። ፓርቲው በጉዳዩ ላይ ከሌሎች የሶማሌ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መነጋገሩንና ሁሉም የምርጫ ካርታውን እንደሚቃወሙት ገልጿል። የሶማሌ ክልል አሁን በምርጫ ካርታው 23 ተወካይ ያለው ሲሆን ከህዝቡ ቁጥርና ከክልሉ ስፋት አንፃር ከ40 ያላነሰ ተወካይ ሊኖረው ይገባ ነበር ብሏል። በጉዳዩ ላይ የምርጫ ቦርድን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።