የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት እንዳመለከተው የሶማሌ ላንድ ድርቅ ሊቀጥል እንደሚችል፣ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሰው በረሃብ ሊመታ እንደሚችል ስጋቱን አሰምቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በሶማልያ የ/ኤንአርሲ/ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቪችተር ሞሰስ በሰጡት መግለጫ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በቂ ዝናብ ስለማይጥል፣ ጨርሶ ላይዘንብም ስለሚችል ቀድሞም በምግብ ዕጥረት የተጎዱት ብዙ ሺህ ሴቶችና ህፃናት ይብሱን ሊጎዱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ዓለምቀፉ ማኅበረሠብ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር እንዲለግስ ጥሪ አሰምተዋል።