የሲዳማ ህዝብ በክልል ደረጃ የመደራጀት ጥያቄ

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በክልል የመደራጀት ጥያቄዎች የደቡብ ኢትዮዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በ10ኛው ጉባኤ በጥናትና በህግ አግባብ እንደሚፈታ ባስቀመጠው ውሳኔ መሰረት ምላሽ እንደሚያገኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ሃምሌ 11 በመጥቀስ ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሃዋሳ ከተማ የሚፈጠር የፀጥታ ችግር እንደማይኖርም ርዕሰ መስተዳደሩ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሲዳማ ህዝብ የምርጫ ቦርድ ሥራ በትዕግስት እንደዲጠባበቅ አሳስበዋል፡፡

የጥያቄው አራማጅ ወጣቶች፣ በምርጫ ቦርድም ሆነ በክልልና በዞኑ መንግሥት መግለጫ እንደማይስማሙ ይልቁንስ ሌላ የትግል አቅጣጫ እንዲጀምሩ የሚያደርጋቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሲዳማ ህዝብ በክልል ደረጃ የመደራጀት ጥያቄ