በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ዕለት በደቡብ ክልል ሼካ ዞን ቴፒ ከተማ «በፀጥታ ኃልይና በተጠርጣሪ ወንጀለኛ መካከል ተፈጠረ» በተባለ ግጭት አንድ የፖሊስ ባልደረባ መሰወቱንና ለማረጋጋት ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አረጋገጠ። ከተማው «አንፃራዊ» ወዳሉት ሰላም መመለሱን ተገለፀ። የከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው መሻሻል ቢኖርም አሁንም ህዝብ በስጋት እንደሚኖርና ከተማውን ለቅቀው የሚወጡም መኖራቸውን ተናገርዋል።