ደቡብ አፍሪካ ያሉ የዚምባብዌ ስደተኞች ሊባረሩ ይችላሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሚኖረው ስደተኛ ትልቁን ቁጥር የያዙት 800 ሺ እንደሚሆኑ የሚነገረው ዜምባቡዌያዊያን ሲሆኑ ብዙዎቹ ለአሥሮች ዓመታት የኖሩ ቢሆንም ሁሉም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸው ተዘግቧል። ብዙዎቹ ዝቅተኛ የሙያ ችሎታ በሚጠይቁ የሥራ መስኮች የተሠማሩ ናቸው።

ባለሥልጣናት ወደ 180 ሺ ለሚደርሱ የዚምባቡዌ ዜጎች “የተለየ ፈቃድ” ቢሰጡም እንደማያድሱላቸው እያስታወቁ ነው፡፡ ለዕድሳቱ የተቀመጠው ቀነ ገደብ እስከሚጠናቀቅበት ሰኔ ድረስ አስፈላጊ የሙያ ክህሎት እንዲኖር የሚጠይቀውን ቪዛ ካላገኙ ለቅቀው መውጣት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል።

የተያያዘው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።