በደቡብ አፍሪካውያን በመጤ ጠልነት መገፋታቸው የገለፁ ስደተኞች በተመድ ደጃፍ ተጠልለዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ስደተኞች፣ “የአገሬው ሰዎች እያሳዩን በሚገኙት ጥላቻ የተነሣ ወደ ሦስተኛ ሀገር እንላክ፤” በሚል ካለፈው ወር ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢሮ ደጃፍ ላይ ተጠልለው ይገኛሉ። ከብሩንዲ፣ ኮንጎ፣ ማላዊ እና ሩዋንዳ የመጡት እነዚኽ ስደተኞች፣ ወደ አገራቸው መመለስ አደገኛ እንደኾነና በደቡብ አፍሪካ ለመቆየትም፣ “የአገሬው ሰዎች እንግዳ ተቀባይ አይደሉም፤” በሚል ወደ ሦስተኛ ሀገር ይላኩ ዘንድ ጠይቀዋል።