የአይሲሲ አባሏ ደቡብ አፍሪካ በፑቲን ላይ የወጣውን የእስር ማዘዣ አንድምታ መመዘን ይዛለች

Your browser doesn’t support HTML5

የአይሲሲ አባሏ ደቡብ አፍሪካ በፑቲን ላይ የወጣውን የእስር ማዘዣ አንድምታ መመዘን ይዛለች

የሄጉ ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት፣ በፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ፣ ከችሎቱ ጋራ የምትተባበርበትን አማራጭ ማጤን ይዛለች፡፡

የፊታችን ነሐሴ ወር በደቡብ አፍሪካ ሊካሔድ በታቀደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ቀደም ሲል ለፕሬዝዳንት ፑቲን ግብዣ ቀርቦላቸዋል፡፡ ፑቲን የተሳትፎ ጥሪውን የሚቀበሉ ከኾነ፣ የእስር ማዘዣውን የማስፈጸም የአባልነት ግዴታ ያለባት ደቡብ አፍሪካ፣ ምን ማድረግ እንዳለባት ማውጣት ማውረድ ይዛለች።

/ዘገባውን ኬት ባርትሌት ከጆሃንስበርግ ያጠናቀረችውን ነው። አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል/