ልዩ ኀይሉ “የመንግሥታትን ህልውና የመጠበቅ ድጋፍ እንሰጣለን፤” በማለት ራሱን በአፍሪካ አህጉር ላሉ ዓምባገነን መንግሥታት እያስተዋወቀ እንደሚገኝ፣ “ሮያል ዩናይትድ ሰርቪስስ” የተሰኘው የብሪታኒያ ተቋም ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ከለንደን የአሜሪካ ድምፁ ዘጋቢ ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ሩሲያ የቫግነርን ስያሜ ስትቀይር በአፍሪካ ተጽእኖዋን የማስፋት ዕቅድ እንደሌላት ገለጸች
Your browser doesn’t support HTML5
ሩሲያ የቫግነር ግሩፕን መጠሪያ “ልዩ የውጭ ተልዕኮ ክፍለ ጦር” በሚል ስያሜ ቀይራለች። በአሁኑ ጊዜ ኢ-መደበኛው ሠራዊት፣ በሩሲያ የወታደራዊ ደኅንነት ክፍል ዕዝ ሥር እንዲውል ተደርጓል።