ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ኢትዮጵያ 137ኛ፣ ኤርትራ የመጨረሻ፣ ሶማሊያ በዓለም እጅግ አደገኛ ሆኑ

የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የፕሬስ ነፃነት ሠሌዳ

ኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕጓን በጋዜጠኞች ላይ አስከፊ በሆነ መንገድ ስለምትጠቀም የጋዜጠኞች አያያዝ ደረጃዋ ቀደም ሲል ከነበረችበት በአሥር መውረዱን ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ድርጅት አስታወቀ፡፡



Your browser doesn’t support HTML5

የ2013 የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ መግለጫ


የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች

ኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕጓን በጋዜጠኞች ላይ አስከፊ በሆነ መንገድ ስለምትጠቀም የጋዜጠኞች አያያዝ ደረጃዋ ቀደም ሲል ከነበረችበት በአሥር መውረዱን ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ድርጅት አስታወቀ፡፡

ዛሬ በወጣው የድርጅቱ ሠንጠረዥ ኤርትራ ከ179 ሃገሮች 179ኛ ሆናለች፡፡
ባለፈው የአውሮፓ ዓመት ብቻ 18 ጋዜጠኞች የተገደሉባት ሶማሊያ በዓለም እጅግ አደገኛዋ ተባለች፡፡

አምብሯዝ ፒየር - የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊ


ሃሣብን በነፃነት በመግለፅ እና በፕሬስ ነፃነት በኩል ምሥራቅ አፍሪካ በተለይ የአፍሪካ ቀንድ ከአጠቃላዩ አህጉር እጅግ አሳሳቢው መሆኑን በምኅፃር አርኤስኤፍ ወይም ራፖርቶር ሣን ፍሮንቲዬ ወይም ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ዋና ፅሕፈት ቤቱ ፓሪስ-ፈረንሣይ የሚገኘው ዓለምአቀፍ ቡድን የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊ አምብሯዝ ፒየር ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ቡድኑ ዛሬ ባወጣው የአውሮፓ 2013 ዓመት የፕሬስ ነፃነት ሠንጠረዡ ላይ አርትራ የመጨረሻዋ መሆኗን የገለፁት አምብሯዝ ፒየር “…አንድም የግል ፕሬስ የሌለባት፣ በአፍሪካ ትልቋ የጋዜጠኞች እሥር ቤት…” ሲሉ ጠርተዋታል፡፡

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም ከሽብር ፈጠራ ጋር በተያያዘ አሥራቸው የነበሩ ሁለት ስዊድናዊያን ጋዜጠኞችን ባለፈው መስከረም መልቀቋ እንደ በጎ ዜና ቢሰማም ለሃገሪቱ ጋዜጠኞች ግን ሁኔታው አሁንም ከባድ መሆኑን አምብሯዝ ገልፀዋል፡፡

“… በዚህች ሃገር ውስጥ ያለው ችግር ባለሥልጣናቱ ፀረ-ሽብር ሕጉን የሚጠቀሙበት የመረጃ ነፃነትን ለመገደብ ጉዳይ ነው…” ብለዋል አምብሯዝ ፒየር ስለኢትዮጵያ በሰጡት መግለጫ፡፡

የፍትኋ ርዕዮት ዓለሙ፣ የአውራምባ ታይምሱ ውብሸት ታየ፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከሶማሊያ ይዘው የወሰዷቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ሳልህ ኢድሪስ ጋማ እና ተስፋልደት ኪዳኔ ተስፋዝጊ፣ እንዲሁም ሃሣቡን በኢንተርኔት የሚገልፀው ብሎገኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የሪፖርተር ሳን ፍሮንቲዬ የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊው አምብሯዝ ፒየር አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ፡፡