የኮንሶ ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲሉ አንድ የሕዝብ ተወካይ ገለጹ

  • መለስካቸው አምሃ

ፋይል

ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፍጽመዋል ሲሉ አንድ የሕዝብ ተወካይ ነኝ ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።

በጥቃቱ አያሌ ቤቶች መቃጠላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ብዙ ሰዎችም የት እንደደረሱ እንዳልታወቀ ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ ወ/ት ሂክማ ከይረዲን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ቃል ቢገቡም በስብሰባ ምክንያት ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኙ አልቻሉም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኮንሶ በነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲሉ አንድ የሕዝብ ተወካይ ገለጹ