ቪኦኤ - ከሬኔ ለፎር ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ የመጨረሻ ክፍል
Your browser doesn’t support HTML5
ከሠሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪካ ሃገሮችን በተመለከተ በሚያደርጓቸው ምርምሮችና ዘገባዎች በዋናነት ከሚታወቁት ተንታኞች አንዱ የሆኑት ሬኔ ለፎር በቅርቡ “መለስ ከመቃብር እየገዙ ነው። ግን እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ፅሁፍ አስነብበዋል፡፡
ሬኔ ለፎር ከቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሰሞኑን የተሰጠውን ሦስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ፡፡
“በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች የመንግሥቱን ሥልጣን እንደገና እየተቆጣጠሩ ናቸው” በማለት ያብራሩበትንና ተዛማጅ ጥያቄዎችን የመለሱበትን የመጀመሪያ ክፍል ቀደም ሲል አቅርበናል።
የመጨረሻውን ክፍል ያዳምጡ፤ ቆንጂት ታየ ነች ያቀናበረችው።