የራያ አካባቢ ኗሪዎች አቤቱታ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል በሚደረገው የምርጫ ምዝገባ ላይ ኗሪዎች በግዴታ እንዲመዘገቡ እየተደረገ ነው ሲል የራያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ለምዝገባ ፈቃደኛ ያልሆኑ የራያ አካባቢ ኗሪዎች ላይ እየተፈጸመ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ግን የተባለው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በግዴታ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ የተገደደ ካለ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል ብሏል፡፡