ራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቦታዎች በህወሓት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ ተከትሎ ከራያ ቆቦ የተለያዩ ወረዳዎች እንዲሁም ከአላማጣና ከአጎራባች አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰባ ሺሕ የሚገመቱ ተፈናቃዮች በቆቦ፣ ሮቢት፣ ጎብዬና ወልዲያ ከተሞች እንዲሁም በድሌሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ተፈናቃዮቹ ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መቆጣጠራቸውን ነዋሪዎች እና ፖሊስ ገልጿል።

ከህወሓት በኩል ለሰላም ማንኛውንም ጥረት እንደሚያደርጉ፣ በአንጻሩ ትግራይ ክልል ከበባ ውስጥ መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ ተይዘዋል ስለተባሉት ቀበሌዎችም ሆነ በአዲስ ቅኝና አካባቢዎቹ ተፈጸመ ስለተባለው ዘረፋ የተሰጠ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም፡፡