የራዲዮ መጽሔት ወጎች:- የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት /SEED/ ሃያ አምስተኛ ዓመት፤ የአገር የሙዚቃና የሥነ ግጥም ወጎች

Amharic Radio Magazine Program Banner

የሳምንቱ መገባደጂያ የእሁድ ምሽት የእረፍት ጊዜ የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት ሃያ አምስተኛ ዓመት፤ የአገር የሙዚቃና የሥነ ግጥም ወጎች፤ “ኢትዮጵያ ትቅደም” በንጉሴ አክሊሉ የአዲስ አበባ የድምጽ መስኮት እና ሌሎች ወጎች

የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት በሰሜን አሜሪካ፤ በእንግሊዝኛ ምሕጻረ ቃሉ - SEED (ማኅበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ) በሃያ አምስተኛ ዓመት የኢዮ-በልዩ ክብረ-በዓሉ ከሥነ ጥበቡ ዘርፍ፥ ቴዲ አፍሮን፥ ለምን ሲሳይን፥ እና አንጋፋውን ድምጻዊ መሃሙድ አህሙድን፤ በበጉ አድራጎት ሥራቸው የገዳሙን አገልጋይ አባ ከፍ ያለው አበራን፤ በዩናይትድ ስቴትስ ለድሆች ነጻ ሕክምና በመስጠትና በሌሎች መልካም ምግባሮቻቸው የሚታወቁትን ዶ/ር አምባቸው ወረታን፤ “ሃኪሞች ለአፍሪቃ” የተባለውን የበጎ አድራጎት ተቋም መሥራች አቶ ቴድ ዓለማየሁንና የሕክምና ምርምር ባለ ሞያውን ዶ/ር ዛኪ ሸሪፍን ጨምሮ “ለሕብረተሰብ ጥቅም የሠሩ፤ የማሕበረሰብ ጉዳይ ግድ የሚላቸው” ያላቸውን ሰባት ኢትዮጵያውያን ያከብራል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች “ቅምሻ”

Your browser doesn’t support HTML5

“መቼ ይሆን?!” - የሳምንቱ ምርጥ ግጥም፤ በያሬድ በላይነህ፤

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት በሰሜን አሜሪካ ሃያ አምስተኛ ዓመት ኢዮ-በልዩ

ማኅበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ በተጨማሪም ለኢትዮጵያውያን ሴቶች መብት በመታገል ይታወቁ የነበሩትንና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ዶ/ር ማይገነት ሽፈራውንም በክብር ያስታውሳል። ሁለት የድርጅቱ ቦርድ አባላት ሌሎች ተያያዥ ቁም ነገሮችም በራዲዮ መጽሔት ያጫውቱናል።

ቴዲ አፍሮ ቀጠሮ ለተያዘለት ቃለ ምልልስ በራዲዮ መጽሔት የ‘ጥበብ እና የጥበበኛው መስኮት’ ብቅ ብሎ ከአሜሪካ ድምጽ ስቱዲዮ እንገናኝ ይላል።

Your browser doesn’t support HTML5

ጥበብ እና ጥበበኛው .. ከቴዲ አፍሮ ጋር የተያዘ ቀጠሮ ወግ

ውበት በሴት ገጣምያን ዓይን ወይም ብዕር “የተሻለ ይሳላል” ትለናለች፤ ወጣቷ ገጣሚ ምልዕቲ ኪሮስ።

“መልስ አልባ ጥያቄ”..“ፍቅርና ጃዝ” .. “እረ-አምሳለ” እና ሌሎችም.. ሥነ-ግጥም ለዛና ቁም ነገር ከተታታይ ቃለ ምልልሱ ያገኛሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

“ውበት” በሴት ገጣምያን ዓይን ... ወጣቷ ገጣሚ ምልዕቲ ኪሮስ።

ንጉሴ አክሊሉ በአዲስ አበባ የድምጽ መስኮቱ “አሜሪካ ትቅደም” በሚለው የፕሬዝዳንት ትራምፕ መርህ ቃል .. “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚለው ሃረግ እና እሳቤ ከአርባ ሦሥት ዓመታት በኋላ ታወሰኝ” ይለናል።

Your browser doesn’t support HTML5

“ኢትዮጵያ ትቅደም” እና “አሜሪካ ትቅደም”

Your browser doesn’t support HTML5

የራዲዮ መጽሔት አድማጭ ድምጽ እና የ‘ደህና እደሩ’ ዜማ ግብዣ፤