ፑቲን ሰሜን ኮሪያን በመጎብኘት ላይ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ረቡዕ ፒዮንግያንግ ሲገቡ ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ፑቲን ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋራ የተገናኙ ሲሆን፣ ከምዕራቡ ዓለም ጋራ ፍጥጫ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ሃገራት ግንኙነታቸውን ይበልጥ የተቀራረበ ለማድረግ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።