እስር እንደ ‘እምቢተኝነት’ አቋም ማሳያ ዘይቤ?

የኢትዮጵያውያን “የጋራ ግብረ-ኃይል” የተባለው ቡድን ባለፈው ቅዳሜ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ባካሄደው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያውያኑ ውጭ የተለየ ትኩረት ስቧል።

የተቃውሞ እንቅስቃሴውን በማካሄድ ላይ ሳሉ “ሕግ ተላልፋችኋል” በሚል በጊዜው የታሰሩት ሁለት ሰዎች በትላንትናው እለት በነጻ መለቀቃቸው ተዘግቧል።

እስሩ በመሠረቱ “በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ነው” ላሉትና ለተቃውሞ ለወጡበት ዋና ጉዳይ ትኩረት ለመሳብ ታልሞ የተከናወነ መሆኑንም አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

አቶ ከባዱ በላቸው ከረሃብ አድማ እስከ ሰብዓዊ መብት ሙግቶች በዋሽንግተንና አካባቢው በሚካሄዱ መሰል የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በሥፋት ከሚታወቁ ኢትዮጵያውያን አንዱ ናቸው። በዋሽንግተኑ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደጋጋሚ የተስተዋለውን መታሰርን ለተነሱበት ዓላማ ማስፈጸሚያ ዓይነተኛ የትኩረት መሳቢያ መንገድ ያደረገውን በዚህ በእምቢተኝነት አቋም ማሳያ ዘይቤ ዙሪያ ሃሳብ ሰንዝረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

እስር እንደ ‘እምቢተኝነት’ አቋም ማሳያ?