የካንሰር ሕክምና መሻሻሎችን እያሳየ እንደኾነ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ፣ በሞሊኪውላር እና ሴሉላር ባዮሎጂ፣ በካንሰር ሴሎች ውስጥ የፕሮቲኖች እድገት ላይ ትኩረት አድርገው የሚመራመሩት እንግዳ ሐጎስ፣ የካንሰር ሕክምና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን እያሳየ እንደኾነ ይናገራሉ፡፡

ተማራማሪው ፕሮፌሰር እንግዳ፣ እስከ ዛሬ ወደ 160 የሚኾኑ ተማሪዎችን አሠልጥነው እስከ ዶክትሬት ደረጃ የደረሱ ባለሞያዎችን ማፍራታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ባላፈው ሳምንት፣ ከኮልጌት ዩኒቨርስቲ፣ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ፕሮፌሰር እንግዳ፣ ውጣ ውረድ በበዛበት የግል ሕይወታቸው እና በካንሰር ሕክምና ላይ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ያደረጉትን አጭር ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡