የአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች ቅሬታቸውን ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በቃሊቲ እሥር ቤት የረሀብ አድማ ላይ ያሉትን የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ፍርድ ቤት ወደ ወሰነላቸው ሕክምና እየወሰዱ ሳሉ በፀጥታ ኃይሎች መከልከላቸውን የበጎ ፍቃደኞች የህክምና ቡድኑ ገልጿል። የፍርድ ቤት የህክምና ትዕዛዙ ለአራተኛ ጊዜ የወጣና አሁንም የተጣሰ መሆኑን የተከሳሾች ጠበቆች ገልፀዋል። በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።