የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ላይ የጥላቻ እና አጸያፊ ንግግሮች-የኢትዮጵያውንን ቀጣይ ጊዜ ፈተናዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛዎች ላይ የሚሠራጩ የጥላቻ እና በአንድ ሰው የብሔር እና ሌሎች ማንነቶች ላይ የሚሰነዘሩ አጸያፊ ንግግሮች፣ ከወዲሁ የማይገቱ ከኾነ፣ ለኢትዮጵያውያን ቀጣይ ጊዜ ፈተና እንደሚኾኑ፣ አንድ ምሁር አሳሰቡ።

በሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶር. ዘነበ በየነ፣ ችግሩ ከመሠረቱ ታውቆ መቀረፍ እንዲችል፣ እያንዳንዱ ግለሰብ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባው መክረዋል።

ከዶ/ር ዘነበን በየነ ጋራ የተደረገው ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።