የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢትዮጵያ ጉብኝት

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ በኢትዮጵያ ባደረጉት የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንት ሩቶ በትዊተር ገጻቸው “ውይይቱ የሁለቱ ሀገራት የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነበር” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የላሙን ወደብ ለደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል እንደ መነሻ ወደብ እንድትጠቀም ፕሬዚዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን መጠየቃቸውንም ጽ/ቤታቸው ገልጿል፡፡

አዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሩቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሆነው፣ በቅርቡ በኢትዮጵያ የስልክ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የኬንያውን ሳፋሪኮም ኩባንያ ሥራ በይፋ ማስጀመራቸውንም በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የአንድ ቀን ጉብኝት አጠናቅቀው ዛሬ አመሻሽ ላይ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡