ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና ወጣት አፍሪካዊያን እንግዶቻቸው

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
የዋሽንግተኑ የወጣቶች ክሕሎት ማበልፀጊያ መርኃግብሩ በማንዴላ ስም ተሰየመ፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለወጣት አፍሪካዊያኑ መሪዎች ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና ወጣት አፍሪካዊያን እንግዶቻቸው

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ተመርጠው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተጋበዙ 500 ወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች፣ ሰኞ፣ ሐምሌ 21/2006 ዓ.ም ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል።

የአፍሪካን የፖለቲካ መሪዎች በሚቀጥለው ሣምንት ለውይይት የጋበዙት ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ “ከአፍሪካ ሀገሮችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት ላይ የተመሠረቱ ግንኙነቶችን ማድረግ ተገቢ ነው” ሲሉ ለወጣቶቹ ገልፀዋል።

የዋሽንግተኑ የወጣቶች ክሕሎት ማበልፀጊያ መርኃግብሩ በማንዴላ ስም ተሰይሟል

“ለዚህ የአፍሪካና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ዋልታዎቹ ወጣቶች ናቸው” ብለዋል።

ወጣቶቹ ፕሬዝደንት ኦባማን ከማግኘታቸው በፊት ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪና ከተወካዮች ምክር ቤቱ /ከኮንግረሱ/ አባላትም ጋር ተወያይተዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡