ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአቡነ መርቆርዮስ ደብዳቤ ፅፈው ሠረዙት

ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ

የቪኦኤ ውይይት ከፕሬዚዳንት ግርማ ጋር




Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአቡነ መርቆርዮስ ደብዳቤ ፅፈው ሠረዙት


ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአቡነ መርቆርዮስ የላኩት ደብዳቤ - ገፅ 1 ፤ በጉልህ ለማየት ምሥሉን ይጫኑት፤ ይበልጥ ለማጉላት እንደገና ይጫኑት


ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአቡነ መርቆርዮስ የላኩት ደብዳቤ - ገፅ 2 ፤ በጉልህ ለማየት ምሥሉን ይጫኑት፤ ይበልጥ ለማጉላት እንደገና ይጫኑት


4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ “ከነ ሙሉ ክብራቸውና ማዕርጋቸው ወደ አገራቸው እንዲገቡና መንበራቸው ላይ እንዲሆኑ” የሚጋብዝ፣ ከኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የተፃፈ ደብዳቤ በማግኘታችን እውነት ስለመሆኑ ወደፕሬዚደንቱ ስንደውል፣ ፕሬዚደንት ግርማ «እውነት ነው፣ እኔ ነኝ የፃፍኩት» ብለው አረጋገጡልን።

አቡነ መርቆርዮስ


የስልኩ ጥሪ ብዙም ጥራት ስላልነበረው እንደገና ስንደውል ደግሞ ቀደም ሲል ደብዳቤውን የፃፉት ሰዎች አሣስተዋቸው መሆኑን ጠቁመው የሻሩት መሆናቸውን ገለፁልን፡፡

ሁለቱም ውይይት ላይ ድምፃቸው አለ፤ የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ።