በኪነ ጥበብ ሞያተኞችና ሥራዎች ላይ የበረታው ፖለቲካዊ ጫና እንዲቆም ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኪነ ጥበብ ባለሞያዎች እና የጥበብ ሥራዎች ላይ፣ “ወከባ እና እስር እየፈጸመ ነው፤” ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ፡፡

ዋና ዲሬክተሩ አቶ ያሬድ ኀይለ ማርያም፣ ፖለቲካዊ ሽሙጥ አላቸው የተባሉ ቴአትሮች እንዳይታዩ መታገዳቸውንና ባለሞያዎችም ስለመታሰራቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ይኸው ወከባ እና እስራት እንዲቆምም ተቋማቸው መንግሥትን በመግለጫ ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ላይ መጻሕፍትን የጻፉት ዶክተር እንዳለ ጌታ ከበደ በበኩላቸው፣ በጥበብ ሥራዎች ላይ ያለው ፖለቲካዊ ጫና፣ “ከትላንት የቀጠለ ነው፤” ሲሉ ይኮንናሉ፡፡ ይህም፣ ሞያው ለሀገር እድገት እና ለውጥ እንዲውል ከማሰብ ይልቅ፣ ለፖለቲካዊ ድጋፍ ብቻ እንዲያገለግል ከሚፈልግ አስተሳሰብ የሚመነጭ ችግር እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡