የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሰሞኑ የአማራ ክልል ዞኖች ሁከት

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች አዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች ውስጥ ጥር 13 / 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሠዓት አካባቢ ጀምሮ የተፈፀመውን ግድያ ያወገዙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርዎች ድርጊቱን ፈፅመዋል በተባሉት ማንነት ላይ ግን የተለያየ አቋም አንፀባርቀዋል።

መኢአድ፣ ኢሕአፓና እናት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ መንግሥቱ በሽብር ቡድንነት የፈረጀውና ባለሥልጣናቱ ‘ሸኔ’ የሚሉት፤ “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን “ንፁሃን ዜጎችን ገድሏል” ሲሉ ወንጅለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው መግለጫ ደግሞ ለጥቃቱና ለግድያዎቹ የአማራ ልዩ ኃይልንና ፋኖን ተጠያቂ አድርጓል።

የአማራ ክልል መንግሥት "ፀረ ሰላም" ሲል የገለፃቸውን ኃይሎች ይህንኑ በኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ ጀውሃ ቀበሌ በሚገኘው የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ሲል እንደሚክስስ ተዘግቧል።

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና ሸኔ በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው ድርጅት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ሠራዊታቸው በአካባቢው እንደሌለ በመግለፅ ውንጀላውን አስተባብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።