ሕዝቡ ባለቤቱ በማይታወቅና በማህበራዊ ድረ-ገፅ ከሚመራ ሰልፍ ጥሪ ራሱን እንዲቆጥብ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አሳሰቡ።
አዲስ አበባ —
መንግሥት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን ለመወጣት ህገ-ወጥ ድርጊቶችን የመግታት ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
ፋና ብሮድካስት ኮረፐሬሽን ባሰራጨው ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተለያዩ እና ወቅታዊ ጉዳዮች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መላው ሕዝብ ችግሮቹን በዲሞክራሲያዊና በሰለጠነ አገባብ መፍታት የሚችልበት ሰፊ እድል እንዳለው ገልጸው ባለቤቱ በማይታወቅ እና በማህበራዊ ድረ-ገፅ ከሚመራ ህገ-ወጥ ሰልፍ ጥሪ ራሱን እንዲቆጥብ አሳስበዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ሕዝብ ባለቤቱ ባልታወቀ ሰልፍ እንዳይወጣ ኃይለማርያም አስጠነቀቁ