“የሰላም አልማዝ” በሥድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

Your browser doesn’t support HTML5

በትልቅነቱ ከዓለም አሥራ አራተኛ የሆነው እና ሲየራሊዮን ውስጥ የተገኘው አልማዝ ኒው ዮርክ ላይ ከሥድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሸጠ፡፡ ሴራሊዮን ከአልማዙ ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ ለልማት ዕቅዶች ማካሄጃ ይውላል ብላለች። ሀገሪቱ ባለሰባት መቶ ዘጠኝ ካራቱን ያልተከርከመ አልማዝ ጨረታ ላይ ስታወጣው የአሁኑ ሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው ግንቦት ወር ዋና ከተማዋ ፍሪታውን ላይ “ከሠባት ሚሊዮን በላይ ልክፈል ያለ” ተጫራች ቀርቦ አያዋጣኝም ብላ ትታዋለች።