የኦሮሞና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ወንድማማችነት ጉባዔ በአዳማ
Your browser doesn’t support HTML5
“ለግል ጥቅማቸው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ” ባሏቸው የሱማሌ ክልል አመራር አባላት አድርሰዋል ላሉት ችግር እና ሥቃይ ማዘናቸውንና ይቅርታም እንደሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ኡመር አስታወቁ:: የኦሮሞና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ወንድማማችነት ጉባዔ ዛሬ አዳማ ከተማ ላይ ተካሂዷል። በጉባዔው ላይ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራር አባላት፣ አባገዳዎችና ኡጋዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ከተለያዩ የየማህበረሰቡ ክፍሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ተሣትፈዋል።