ከምስራቅ ሸዋ ቡልቡላ ከተማ ጥቃት ጋር በተገናኘ ሦስት ሰዎች በቁጥጥር ዋሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ምስራቅ ሸዋ ዞን ቡልቡላ ከተማ ቅዳሜ መጋቢት መጋቢት 10 /2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአካባቢ ሚሊሺያ አባላት ምርቃት ላይ የተከሰተውን ቦምብ ፍንዳታን ተከትሎ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአካባቢው አስተዳደር አስታወቀ።

አቶ መሐመድ በሪሶ የአዳሚ ጅዶ ኮቦልቻ ወረዳ አስተዳዳሪ በቅዳሜው ጥቃት የ12 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸዉን ተናግረዋል።