በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እሥራቶች መካሄዳቸውን የኦፌኮ መሪ ገለፁ

አቶ በቀለ ነጋ - የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ



Your browser doesn’t support HTML5

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እሥራቶች መካሄዳቸውን የኦፌኮ መሪ ገለፁ


ነቀምቴና ሃረማያን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሎች ትናንትና ዛሬ በሰዉ ላይ ድብደባና እሥራት እየፈፀሙ ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ተናግረዋል፡፡

አቶ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ በምዕራብ ሸዋ በግንደበረትና ጀልዱ፤ እንዲሁም ምሥራቅ ሸዋ አርሲ ነገሌ ተማሪዎች እየተያዙ መታሠራቸውን በወለጋ፤ ነቀምቴም ብዙ ሰው እየተያዘ መታሠሩን ገልፀዋል፡፡

ትናንት ደግሞ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ አሥር ተማሪዎች ከየማደሪያቸው በፖሊሶች መወሰዳቸውን አቶ በቀለ አክለው ገልፀዋል፡፡

ፓርቲያቸው ሁኔታውን ለመንግሥት ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ከመንግሥት አካላት ስለጉዳዩ ማብራሪያ ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢደረጉም ለጊዜው አልተሣካም፤ ምላሽ በተገኘ ጊዜ እናወጣለን፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡