ጦርነቱ እንዲቆም ሦስት ፓርቲዎች አሳሰቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ያገረሸው የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሦስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዳግም ጥሪ አቀረቡ።

በአዲስ አበባና በኦሮምያ ክልል ወሰን መካለል ጉዳይ ላይ ሃሳባቸውን ለመስጠት በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በጋራ የተናገሩት የእናት ፓርቲ፣ የመኢአድና የኢህአፓ ተወካዮች “መንግሥትና ህወሓት ችግሩን ለመፍታት ያሉትን የሰላም አማራጮች ሁሉ እንዲጠቀሙ” ጥሪ አቅርበዋል።