ኦብነግ ኢትዮጵያ ገባ

የኦብነግ ታጣቂዎች አሥመራ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ሲሣፈሩ /ምንጭ - የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኔስቴር ዌብሳይት - shabait.com/

ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።

የግንባሩ ሠራዊት ዛሬ ከአሥመራ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች ተነስቶ ኢትዮጵያ መሄዱን ገብቷል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለመቀጠል ልክ የዛሬ ወር ጥቅምት 11/2011 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አሥመራ ላይ በገባው ውል መሠረት መሆኑት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በሻባይት የዌብ ገፁ ላይ አሥፍሯል።

የሻባይት ዜና እንደሚናገረው የኢትዮጰያ መንግሥት የሃገሪቱን ሕገመንግሥት እንደሚያከብር፣ የኦጋዴንን ችግር ከሥረ-መሠረቱ ፈትሾ ፍሬ ያለው ውይይት የሚያዘጋጅና መፍትኄ የሚያፈላልግ የጋራ ኮሚቴ እንደሚያቋቁም ቃል ገብቷል።

የኦብነግን ታጣቂዎች አሣፍረው ዛሬ ረፋድ ላይ ከአሥመራ የተነሱት ሁለት አይሮፕላኖች ጂግጂጋ ማረፋቸውን የግንባሩ ቃል አቀባይ አብዱልቃዲር ሃሰን ሂርሞጌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።

የኦብነግ አርማ

ከኤርትራ ከገቡት ሌላ ግን ግዙፍ ቁጥር ያለው የግንባሩ ተዋጊ ኢትዮጵስያ ውስጥ በሽምቅ ውጊያ ላይ ተሠማርቶ መቆየቱንም አቶ አብዱልቃድር ተናግረዋል።

ኦብነግ ላለፉት ሰላሣ አራት ዓመታት ሲፋለም መቆየቱን የተናገሩት ቃል አቀባዩ አብዱልቃድር የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴው ተቋቁሞ ዘላቂ መፍትኄ እስኪገኝ ትጥቅ ስለመፍታት ጉዳይ ለመነጋገር ጊዜው ገና እንደሆነ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦብነግ ኢትዮጵያ ገባ