የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት ከናይሮቢ አፍኖ ወስዷቸው ነበር ያላቸው ሁለት ተደራዳሪዎቹ ከትናንት በስተያ - ሰኞ መለቀቃቸውን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር - ኦብነግ አስታውቋል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት ከናይሮቢ አፍኖ ወስዷቸው ነበር ያላቸው ሁለት ተደራዳሪዎቹ ከትናንት በስተያ - ሰኞ መለቀቃቸውን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር - ኦብነግ አስታውቋል፡፡
እነዚህ ከአንድ ዓመት ከአራት ወራት በኋላ የተለቀቁት ሁለቱ የግንባሩ ባለሥልጣናት ሱሉብ አህመድ እና አሊ ሁሴን የሚባሉ ሲሆኑ ሁለቱም አሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጤና እንደሚገኙ የግንባሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢንፎርሜሽን ቢሮ ኃላፊ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ሰዎቹ የተለቀቁት በኬንያ መንግሥትና በሌሎችም ዓለምአቀፍ ጥረቶች መሆኑን አቶ ሃሰን ገልፀዋል፡፡
አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ቀደም ሲል ለቪኦኤ ሰጥተውት በነበረ መግለጫ ሰዎቹ እጃቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ሰጡ እንጂ በክሡ ላይ እንደሚባለው አፈና ወይም ጠለፋ አልተካሄደባቸውም ብለው ነበር፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡