ከሜዲቴራኒያን ባህር የተረፉ ከአንድ ሺህ በላይ ፍልሰተኞች ጣልያን ወደብ ደረሱ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሊብያ የተነሱና ትናንት ዕሁድ በእርዳታ ደራሾች ከሜዲቴራኒያን ባህር የተረፉ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሆነ ፍልሰተኞች ከጣልያን ሲቺሊያ ደሴት ወደብ ላይ ደረሱ፡፡ ፍልሰተኞቹን ዛሬ የጣልያኗ ካታኒያ ወደብ ላይ ያደረሰችው አንዲት የጀርመን ባሕር ኃይል መርከብ መሆኗ ታውቋል፡፡