ተቃዋሚ ፓርቲዎች እስራትና ወከባ ደረስብን አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ በኦሮምያ ክልል ውስጥ መንቀሳቀስ አልቻንም አባሎቻችንም በገፍ እየታሰሩብን ነው አሉ። የኦሮምያ ክልል በበኩሉ ፓርቲዎቹ እያጋጠመን ነው ያሉትን ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመንግሥት ማሳወቅ አለባቸው ሲል አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አቤቱታ ማቅረባቸውን ገልፆ ለሚመለከተው ባለሥልጣን ደብዳቤ መፃፉን አስረድቷል።