የፀጥታ ኃይሎች ጋዜጣዊ መግለጫቸውን እንዳቋረጡ አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር መሆናቸውን የገለፁት አቶ ዳውድ ኢብሳ ትናንት በቤታቸው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሲሰጡ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ግቢው ገብተው መግለጫው እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን እና ጋዜጠኞቹንም ይዘው ሄደው ማሰራቸውን አስታወቁ። ክሱን በተመለከተ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልስ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ማግኘት አልቻልንም።