የአቶ ኦልባና እሥራት ተቀነሰ

  • መለስካቸው አምሃ

አቶ ኦልባና ሌሊሣ እና አቶ በቀለ ገርባ




Your browser doesn’t support HTML5

የአቶ ኦልባና እሥራት ተቀነሰ


የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአቶ ኦልባና ሌሊሳን የእሥር ቅጣት ከ13 ወደ 11 ዓመት ዝቅ እንዲል ወሰነ።

የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦልባና “የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካትና የኦነግን ተልዕኮ በማሣካት” በሚሉ ክሦች የበታች ፍርድ ቤት የ13 ዓመታት እሥራት የፈረደባቸው መሆኑ ይታወቃል።

አቶ ኦልባና ፍርድ ቤቱ የፈረደባቸው “ያለአንዳች ጥፋትና ያለ በቂ ማስረጃ ነው” በማለት በነፃ እንዲለቀቁ፣ አልያም የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸው ከግምት ገብቶ በአነስተኛ ቅጣት እንዲታለፉ ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።

በተያያዘ ዜና በተመሣሣይ ወንጀል ከአቶ ኦልባና ጋር የተከሰሱት የአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ በዚሁ ፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ ታውቋል።

አቶ በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር እንደነበሩ ይታወሣል።

በአቶ ኦልባና ሌሊሳ ጉዳይ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ያሳለፈውን ውሳኔ የሚመለከተውን ዘገባ የያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ።