በኦሮሚያ ክልል በርካታ ሰዎች በምሸት እየተያዙና ወዳልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ነው ሲል የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ አስታወቀ።
አዲስ አበባ —
መንግሥት ደግሞ ከሕግ ውጪ ማንም የታሰረ ሰው የለም ብሏል።
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት በኦሮምያ ክልል የሚካሄደው ማሰር እና ማሳደድ ቀጥሏል።በተለይ በምሽት የሚወሰዱት ሰዎች የት እንደታሰሩ እንኳን ለማወቅ እንዳልተቻለ አብራርተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ በኦሮምያ ክልል ከተካሄደ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ከታሰሩ ሰዎች ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑ መፈታታቸውን መረጃ እንዳላቸው የኦሮሞ ፈደራሊስ ኮንግረስ አቶ ሙላቱ ገመቹ አስታውቀዋል።
አንድም ሰው ሲፈታ ደስ ይለናል ያሉት ምክትል ሊቀ መንበሩ መንግሥት የቀሩትንም በሙሉ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ የተካሄደውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተከትሎ የታሰሩት ሰዎች ቁጥር ወደ 10,000 ሊጠጋ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ብዙ ሺህ ታሳሪዎች በተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙም ምክትል ሊቀመንበሩ አብራርተዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5