በወልድያ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ኦፌኮ አወገዘ

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

በወልድያ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ስልጣን በአቋራጭ መንገድ ለመያዝ በሚያሴሩ ኋይሎች የተደረገ ክፉ አድራጎት ነው ሲል፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ኮነነ። በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ለዚህ አስከፊ ድርጊት አፀፋ እንዳይፈፀምም ተማፀነ። የድርጅቱ የሥራ አስፋፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ በድርጊቱ ወደ ነበሩበት የሥልጣን ዘመን ለመመለስ ያለሙ አካላት እጅ አለበት ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።