ኦባማ ሲናገሩ በኢትዮጵያዊ “ነፃነት ለኢትዮጵያ” ጩኸት ተደናቀፉ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

አበበ ገላው




Your browser doesn’t support HTML5

ኦባማ ሲናገሩ በኢትዮጵያዊ “ነፃነት ለኢትዮጵያ” ጩኸት ተደናቀፉ



የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በተለያዩ ጊዜዎችና ሥፍራዎች ንግግር ሲያደርጉ አድማጮች በጩኸት ግራ ሲያጋቧቸው ታይቷል።

ፕሬዘዳንቱ ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ ፆታ ግንኙነትና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ ሲናገሩ ተቃዋሚዎች ንግግራቸውን በጫጫታ አደናቅፈዋቸው እንደነበር ይታወቃል።

ባለፈው ሐሙስ፤ ሚያዝያ 25/2006 ዓ.ም ሳን ሆዜ - ካሊፎርኒያ ውስጥ በአንድ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ላይ ሲናገሩ ግን ከዚህ በፊት ከታዩት ሁሉ ለየት ያለ ጉዳይ ተነስቷል። የኢትዮጵያ ጉዳይ።

ከታዳሚዎቹ መካከል አንድ ሰው ተነስቶ «ፕሬዘዳንት ኦባማ! ነፃነት ለኢትዮጵያ!» ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ። ሚስተር ኦባማም መልስ ሰጡት።

ያ ሰው ማን ነበር? ሰሎሞን ክፍሌ በስልክ አግኝቶታል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን የ«ዲሞክራሲ በተግባር» ቅንብር ያዳምጡ፡፡